Weekly Devotion

 

“በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል። ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን!” (1ጴጥ. 5፥10)                         በዚህ ክፍል “የጸጋ ሁሉ አምላክ” የሚለውን አስተውል። እንዲሁም “በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ” የሚለውን…

“ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች። እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት” (ሐ.ሥ. 9፥40-41) ዛሬ የሞተብህ ነገር አለ? የሞተብሽ ነገር ምንድነው? ምንም መፍቲሄ ሊሰጡ ከማይችሉ ሰዎች ተቀምጠህ ሬሳን እያየህ ይሆናል። ሬሳን በፊትህ አኑረህ እያለቀስህ…

“ኢያሱም ካህናቱን፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ ብሎ ተናገራቸው የቃል ኪዳኑንም ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ” (ኢያሱ 3፥6) እስራኤል ዮርዳኖስን ለመሻገር ታቦቱን ማስቀደም ነበረባቸው። እግዚአብሔር ይህንን ትዕዛዝ ለካህናቱ የሰጠውም ታቦቱ የእግዚአብሔር አብሮነት ተምሳሌት ስለ ነበር ነው። ሌላው ታቦቱ ከፊት እንዲመራቸው የሆነው ሃሳባቸው፣ ትኵረታቸውና አመለካከታቸው ወደ አምላካቸው እንዲሆን ነበር። ታቦቱን መከተልም በአዲስ መንገድ የመሄድ…

“ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ” (ኢያሱ 3፥5)              እስራኤላውያን ይርዳኖስን እንዲሻገሩ የተመረጠው ጊዜ የሚገርም ጊዜ ነበር፣ ወንዙ በጣም የሚሞላበት ወቅት! ለምን? እግዚአብሔር ዛሬም እንዲሁ ችግሮች ሲሞሉ (ሲበዙ) አልያም ብዙ ጠበቅሁት፣ ብዙ ጸለይኩበት የምንላቸው ነገሮች ሲሞሉ እንድንሻገር ያደርገናል። ሲያሻግረን ደግሞ አድርቆ እንጂ አጕድሎ አይደለም። እስራኤል ዮርዳኖስን የተሻገሩት ተከፍሎና ደርቆ…

ከሰጢም ተነሱ፣ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፣ ተስፋውን ውረሱ” (ኢያሱ 3)             እስራኤል ዮርዳኖስን ሳይሻገሩ በሰጢም ብዙ ጊዜ ቆይተዋል። በቆይታቸው ጊዜም ብዙ ነገር ደርሶባቸዋል። ለምሳሌ ከሌሎች ጋር ተደባለቁ፣ የሌሎችን ባህል በመሃከላቸው አስገቡ፤ ተስፋቸውን ጣሉ (ተዉ)፣ ብዙ ኀሳረ-መከራን አዩ። እኛም ዛሬ እንዲሁ፣ ተስፋችን አርጅቶ፣ የመከራ ጊዜአችንም ረዝሞ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ግን የገባውን ተስፋ ይፈጽማል…

 “እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም ይሄዳሉ፥ አይደክሙም” (ኢሳ. 40፥31) (ከቍ. 23 – 31 ያለውን አንብብ) ሰይጣን ሰዎችን ለማጥቃት ከሚጠቀምባቸው መሣርያዎች አንዱ ተስፋ ማስቆረጥ ነው። ተስፋ ስንቆርጥ ጸልየንም ሆነ ጮኸን እግዚአብሔር የሚሰማን አይመስለንም። እንባቆም ባካባቢው ከነበረው ሥርዓት አልባነትና ቀውስ የተነሣ ተስፋ ቆርጦ ነበርና “አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ…

 

 

 

 

© 2016 Ethiopian Evangelical Church in Toronto
Top
Follow us: